=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ጠፍቶብኝ የአሏህ ሰፊ ችሮታ
ትናንትን የኖርኩት ሆነብኝ ብዥታ።
መጭውንም ጊዜ ሳላውቀው
መኖሬንም ቀጠልኩ ዛሬ ነገ እንደሚል ተስፋ እንደቆረጠ ሰው።
ደስታን ለማጣጣም ስሰራ በርትቼ፤
የተፈጠርኩበትን አላማ ረስቼ፤
ዛሬን ስኖር በኩራት በዝና፤
ለአሄራ መስራቴን ትቼ ስዝናና፤
እኔምላለሁ ፣ እኔምእላለሁ ነገን እቶብታለሁ፤
እሞት እኖር ሳላውቀው ወንጀልን ለመስራት ራሴን አታልላለሁ።
ዩኒቨርሲቲ ስገባ አድርጌ አላለማየን ሂወቴን በደስታ ልመራ፤
በመጠጥ ፣ በዚና ፣ በሙዚቃነና በጭፈራ፤
ነጋዴ ሁኜ ስሰራ ሰዎችን ሳታተልል እንዳይደርስብኝ ኪሳራ።
ባለኝ ነገር መብቃቃት አቅቶኝ እግሬን ስሰድ ወደ ጀሐነም ጋራ፤
ለዱንያዊ ደስታ አጐብድጄ ሃራምን ስሰራ፤
እምጠቀም መስሎኝ ቤተሰቤን ስንድ ዝምድናን ሳጥላላ፤
ሰዎች ራቁኝ አደረጉኝ ቀውላላ።
ቀኔ ጨለማ ለበሰ ፤
ልቤ በፍርሃት ተጠበሰ ፤
ደስታ ሳይሆን ሃዘንና ፍርሃት በውስጤ ነገሰ።
እሺ በጥፋቴ ሰዎችስ ይራቁኝ፤
ግን እንዴት የምበላው ምግብ ጣእሙ ይጥፋብኝ!!!
ያረቢ ጌታየ
መኖሬ ከሆነኝ ቀበኛ ፤
የሰራሁት ስራ ካረገኝ የሸይጧን ምርኮኛ ፤
ይቅር መደሰቴ በሃራሙ መንገድ ፤
ልስራ መልካም ስራ የሚሆነኝን ዘመድ።
ጌታየ አሏህ ሆይ ተቀበለኝ ተውበቴን
እስኪ ሱጁድ ላድርግ ላሳይ ባርነቴን!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|